አማርኛ / Amharic (Ethiopia)

እነዚህ ግብዓቶች የተተረጎሙት በአገልግሎት አጋሮቻችን ነዉ፡፡ እነዚህን ግብዓቶች የምናቀርባቸዉ በነፃ ሲሆን ሌሎችም እንደ እናንተ አውርደዉ እንዲጠቀሙባቸዉ ለሌሎች እንድታጋሯቸዉም ጭምር ነዉ፡፡

These resources have been translated by our ministry partners. We provide these resources to you for free and ask that you would let others know, so they too can download translated re-sources for free from our website.

Truth78 የሚቀጥሉት ትውልዶች እግዚአብሔርን በማወቅ፤ በማክበርና ከምንም በላይ ሀብታቸዉ በማድረግ ተስፋቸዉን በክርስቶስ ላይ ብቻ አድርገዉ ታማኝ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሆነዉ እንዲኖሩ ለማድረግ አትኩሮ የሚሰራ ራዕያ ያነገበ አገልግሎት ነዉ፡፡

ተልዕኳችን ቤተ ክርስቲያንና ቤተሰብ ለተሳካ እና ለተዋጣለት ቀጣዩን ትውልድ ደቀ መዝሙር የማድረግ ተግባር እንዲጣመሩ ማነሳሳት እና ማብቃት ነዉ፡፡

እግዚአብሔርን ማዕከላዊ ያደረጉ፤ በመፅሐፍ ቅዱስ እዉነት የታጨቁ፤ ክርስቶስን የሚያልቁ፤ በመንፈሱ ላይ የተደገፉ፤ በትክክለኛዉ አስተምህሮ መሰረት ላይ ስር የሰደዱ፤ እና ደቀ መዝሙርነትን ማዕከላዊ ያደረጉ ግብዓቶችን እናዘጋጃለን፡፡

ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶችን ለመተርጎም ፍላጎት ካለዎትም ሆነ፤ ስለ ግብዓቶቻችን አጠቃቀም ጥያቄ ካለዎት እባክዎትን በዚህ አድራሻ ይፃፉልን፡፡ [email protected] በተርጓሚዎቻችን ድጋፍ ጥያቄዎቸችሁን ለመመለስ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡

የተፈቀዱ መብቶችን የሚገልፅ መረጃ

Truth78 እነዚህን ግብዓቶች ለቤተሰብ፤ ለቤተ ክርስቲያን፤ ለትምህርት ቤቶች፤ እና የተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲታተሙ እና አገልግሎት ላይ እንዲዉሉ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ ነገር ግን ለሌሎች ድርጅቶች ወይም በርካታ ቤተሰቦች ማስተላለፍም ሆነ ሸጦ ማትረፍ አልተፈቀደም፡፡ ነገር ግን ሌሎችም እነዚህን ግብዓቶች እንዲጠቀሙ እባካችሁ ወደዚህ ድህረ-ገፅ መጥተው እንዲያወርዱ ጠቁሟቸዉ፡፡

ቀናኢነት፤ የሚቀጥለዉን ትውልድ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ማድረግ የሚጠይቃቸዉ 7 መሰጠቶች

ቀናኢነት፤ የሚቀጥለዉን ትውልድ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ማድረግ የሚጠይቃቸዉ 7 መሰጠቶች

በዚህ መፅሐፍ የረጅም ጊዜ መጋቢ እና የTruth78 ተቀዳሚ ዳይሬክተር የሆኑት ዲቪድ ማይክል ከእግዚአብሔር ፍቅር የመነጨ እና ለእርሱው ክብር የሚሆን ግለት እና ትጋትን ያብራራሉ፡፡ ለሚቀጥለዉ ትውልድ ደቀ መዝሙር መሆን የሚያስፈልገዉን ራዕይ የሚቀርፁ ሰባት መሰጠቶችን አቅርበዋል
  1. ቀጣዩ ትውልድ እምነት እንዲኖረዉ የሚያደርግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ራዕይ ማንገብ
  2. በቤተክርስቲያን እና በቤተሰብ መካከል ጠንካራ አጋርነት ማሳደግ
  3. ምሉዕ የሆነውን የቃለ-እግዚአብሔርን ምክረ-ሓሳብ በስፋት እና በጥልቀት ማስተማር
  4. አስደናቂውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማስተማር
  5. አዕምሮን፤ ልብን እና ፈቃድን ለደቀ መዝሙርነት ማስገዛት
  6. በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ጸጋ ላይ በመደገፍ መጸለይ
  7. አምልኮተ-እግዚአብሔር በትክክል ለእግዚአብሔር ክብር የሚያመጣ እንዲሆን ማድረግ
ግብዓቱን ያውርዱ